ቤተክርስቲያን ሆይ ንቂ

ቤተክርስቲያን ሆይ ንቂ
ቤተ ክርስቲያን ከመሰረታትና ሙሉ ባለቤትነት ካለው ከክርስቶስ ተልዕኮ ተሰጥቷት በምድር ላይ ያለች የክር ስቶስ አካል ነች፣ቤተክርስትያን ላለፉ ት 2000አመታት በብዙ ድልና በብዙ ውጣወረድ እንዲሁም በብዙ ችግሮ ች ውስጥ አልፋለች አሁንም እያለፈ ች ነው።ቤተክርስቲያን የሰው አይደለ ችም፣የሐዋርያ፣የፓስተርም የነብይ ም፣ የወንጌ ላዊም የአስተ ማሪም አይደለችም፤ ነገር ግን ሰው ሊያስተ ዳድራት ይችላል፤ እንዲሁም መጽሐ ፍ ቅዱሳችን ቤተክ ርስቲያን ለሰራች ው መልካምም ሆነ እንደ እግዚአብ ሔር ቃል ባልተመ ላለሰችበት ጉዳይ ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ብድራትን እንደምት ቀበል ያስተ ምራል፤ ቤተክ ርስቲያን በአገልግ ሎቷ፣ በአካሄዷ፣ በሃላፊነቷ፣ በተሰጣት የጸጋ ስጦታ ና በተሰጣት መንፈሳዊ ስልጣ ንና ኃይል ጉዳይ በኢየሱስ ክርስቶስ የፍርድ ወንበር ፊት ትቆማለች፣በዚህ የፍርድ ወንበር ፊት ትዳኛለች ትጠየ ቃለች ፣ከዛም እንደስራዋ ታገኛለች፣ያ ማለት ግን ቤተክርስቲያን የምትዳኘ ው በሽልማት ጉዳይ መሆኑ እሙን ነው- ይህ ማለት ቤ/ክ በነጩ ዙፋን ፍርድ ፊት ቆማ አይደለም የምትዳኘ ው፣ 👇
”’ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና።ሮሜ 14 :10
እንግዲያስ እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዚአብሔር መልስ እንሰጣለን። ሮሜ 14 : 12
በራዕይ መጽሐፍ ላይ ሰባት አብያተክ ርስቲያናት ተጠቅሰዋል፣ የኤፌሶን ቤ/ክ፣ ሰምርኔስ ቤ/ክ፣ ጴርጋሞን ቤ/ክ ፣ትያጥሮን ቤ/ክ፣ ሰርዴስ ቤ/ክ፣ የፊልድልፍያ ቤ/ክ፥ሎዶቅያ ቤ/ክ ናቸው።
❄ እነዚህ ሰባቱ አብያተክርስቲያናት በወቅቱ በትንሹ ኢስያ የሚገኙ አጥቢያዎች ነበሩ፤ እያንዳንዳቸው አብያተክርስቲያናት ጠንካራና ደካማ ጎኖች ነበራቸው፣ኢየሱስም ለጠንካራ ጎናቸው ማበረታቻ ለደካማ ጎኖቻቸው ደግሞ ምክር ሲሰጥና ሲገስጽ እንመለከታለን።ለምሳሌ 1 👉የኤፌሶን ቤተክርስቲያን
የኤፌሶን ቤ/ክ ስንመለከት የኤፌሶን ቤ/ክ ለክርስቶስ ስም ስትል ጸንታ የቆመች፣ ሐዋርያት ነን ባዮችን መርምራ አለመሆናቸውን የምታጋል ጥ፣ ፣ያልደከመች ቤ/ክ ነበረች፤ግን የቀድሞ ፍቅሯን ትታለች፣ለዚህም ውድቀቷ ከወዴት እንደ ወደቀች እንድታስብ ንስሐም እንድትገባ የቀደመውን ሥራዋን እንድታደርግ፤ አለዚያ እንደሚመጣ ባት ንስሐም ባትገባ መቅረ ዝዋን ከስፍራው እንደሚወስድ ማስጠንቀ ቂያ ደርሷታል።ራእይ 2:1-5 የኤፌሶን ቤ/ክ በወቅቱ በትንሹ ኤስያ የምትገኝ ከተማ ነበረች፣ ኤፌሶን የንግድና ከሶስቱ የሮም ግዛቶች በጣም ዝነኛ ነበረች፣ኤፌሶን ከተማ የአርጤም ስ ቤተ ጣኦት መገኛ ነበረች(ሐዋ19:21-41)
2 👉ሰምርኔስ ቤተክርስቲያን (ራዕ 2:9)
የሰምርኔስ ከተማ ከኤፌሶን በስተም ዕራብ በኩል በ25ማይል ርቀት ትገኝ ነበር፤በዚህ ከተማ ቤ/ክ ከሁለት ዋና ዋና ችግሮች ጋር ትጋፈጥ ነበር 1ኛ የአይሁድ ክርስትናን መቃወ ምና አይሁድ ያልሆኑ አምልኮተ ንጉስን መቀበላ ቸው ዋና ዋና ችግሮች ነበሩ፤
3👉 የፔርጋሞን ቤተክርስቲያን የፔርጋሞን ከተማ በ1000ጫማ ከፍታ ባለው ከተማ ላይ የተመሰረ ተች ከተማ ነበረች፣ ከተማ ዋ የግሪክ ባህልና ስልጣኔ ማዕከል ነበረ ች፣ ከተማዋ የተለያዩ አይነት ጣእቶች ነበሩ ባት፣ ፔርጋሞን በእባብ ራሱን በመሰለ ጣኦት የተሞላች ከተማ ነበረች፤ አማኞች በዚህ ከተማ ታላቅ ስደትና እምነታቸውን እንዲተው ግፊት ይደረግባቸው ነበር፣ በፔርጋ ሞን ይገኙ የነበሩ አማኞች በእምነ ታቸው ተመስክሮላቸዋ ል የተወቀሰች በትም ነገር አለ አንደኛ በስህተት ትምህርትና በስነምግባር ጉድለት።
ቀጣይ ክፍል
ቤተክርስቲያን ሆይ ንቂ
4,የትያጥሮን ቤተክርስቲያን (ራዕ 2:20-22)⛪
ትያጥሮን በጥንት በሮማውያን የኤዥ ያ ግዛቶች ውስጥ አንዷ የነበረች ባለ ጠጋ ከተማ ነበረች። ይህች ከተማ በአሁኑ ወቅት ቱርክ ነች።
ለዚህች ቤ/ክ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠንካራ እና ደካማ ጎኗን በማንሳት ከደከመችበት ሁኔታ እንድትወጣ አምላካዊ ምክር ሲመክርና ሲገስጽ እናነባለን።
የትያጥሮን ቤተክርስቲያን 5 ዋና ዋና ጠንካራ ጎኖች
1 ፍቅር 2እምነት 3 አገልግሎት 4 ትዕግሥት 5 ታላቅ ስራ
በመቀጠል ኢየሱስ ክርስቶስ የዚህችን ቤ/ክ ሃጢአት/ውድቀት ይጠቅሳል።
”ዳሩ ግን ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተም ረውንና የምታስተውን ያችን ሴት
ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ ”
👉በወቅቱ ሐሰተኛ ነብያቶች፣ጣኦት የሚያመልኩ፣ግልሙትና ውስጥ የገቡ ክርስቲያኖች በቤተክርስትያን ውስጥ ነበሩ።
5,የሰርዴስ ቤተክርስቲያን (ራዕ 3:1)
የሰርዴስ ከተማ በወቅቱ ባለጠጋ የንግድ ከተማ እና በሙስና የምትታወቅ ከተማ ነበረች።የሰርዴስ ቤ/ክ ዋና ችግር 👇
” ሥራህን በአምላኬ ፊት ፍጹም ሆኖ አላገኘሁትምና የነቃህ ሁን፥ ሊሞቱም ያላቸውን የቀሩትን ነገሮች አጽና።”’ የዮ ራእይ 3 : 2
6,የፊልድልፊያ ቤተክርስቲያን
(ራዕ 3:8-9) ⛪
,የፊልድልፊያ ከተማ በፔርጋሞን ህዝቦች የተመሰረተች ከተማ ነበረች ከተማዋ ከዘመናት በኋላ በመሬት መንቀጥቀጥ ልትጠፋ ችላለች፤ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዚህች ቤ/ክ ማበረታቻ እና ዋና ዋና ምክሮችን ይመክራታል።
7,የሎዶቅያ ቤተክርስቲያን(ራዕ 3:16)
የሎዶቅያ ከተማ በባንክ ሴልጣኔና በጥጥ ንግድ እንዲሁም በህክምና ት/ት በተለይ በአይን ኩል ገናና ነበረች፣ የቤ/ክ ዋና ችግር የአቋም ችግር ነበር። ወይ ቀዝቃዛ አልሆነች ወይ ሙቅ/ትኩስ/ አልሆነች።ሌላው የዚህች ቤ/ክ ድክመት ሃብታም ነኝ አንዳች አያስፈልገኝም ባይ መሆኗ ነው፣ ቤ/ክ ይህን ትበል እንጂ ጌታ ኢየሱስ እንዲህ ይላታል
”’ ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥”
የ ራእይ 3 : 17
ከላይ በራዕይ መጽሐፍ ላይ የተመለከትናቸው ሰባቱ አብያተክርስ ቲያናት ምን እንማርባቸዋለን??
1,ፍቅር ላይ ያልተመሰረተ አገልግሎት፣እምነት፣ዕናት፣ትጋት ከንቱ እንደሆነ እንማራለን።
2,ቤተክርስቲያን ለሰራችው ድልም ሽንፈት ከኢየሱስ የምትቀበለው ብድራት እንዳለ መማር እንችላለን።
3,ቤተክርስቲያን ከኢየሱስ ክርስቶስ በተሰጣት አላማ ላይ የሙጥኝ ብላ አላማዋን ከግብ ማድረስ እንዳለባት 4,ቤ/ክ የእምነት ተጋድሎን በሚገባ መታገል እንዳለባት መማር እንችላለን
5,ቤተክርስቲያን በአስተምህሮ፣በአ ካሄዷ፣አቋም ያላት የጸናች መሆን እንዳለባት መማር እንችላለን።⛪
6,ቤተክርስቲያን የትኛውንም አይነት የዲያብሎስ አሰራር መቃወምና መተ ባበር እንደሌለባት ⛪
7,ቤ/ክ ከመንግሥት፣ከቤተሰብ፣
ከግለሰብ የተለያዩ አይነት ተቃውሞ ሊደርስባት ይችላል ቢሆንም ግን ጌታ እንደተናገረን መፍራት እና ወደ ኋላ ማፈግፈግ እንደሌለብን እንማራለን።⛪
8,ቤ/ክ የሃሰት ትምህርቶችን በመቃወም ጤናማው ት/ት መከተል እንዳለባት ያስተምረናል።⛪
9,የተለያዩ አጋንንታዊ ልምምዶች ቤተክርስቲያን ልትቃወም ይገባል ለምሳሌ በፔርጋሞን ቤ/ክ በወቅቱ ፈውስ ለመቀበል በተሳሳተ ት/ት ራሱን አዳኝ ነኝ ብሎ ወደሚጠራው እባብ ይሄዱ ነበር።⛪💢ቤተክርስቲያን መጠንቀቅ ያለባት አደጋዎች
1,ከዘመኑ ሰዱቃውያን
የሰዱቃውያን ታሪካዊ አመጣጥ
ሰዱቃውያን በጌታችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የምድር የአገል ግሎት ዘመን መኳንንቶች፣ ባለጠጋና የፖለቲካ መሪዎች ነበሩ፤በወቅቱ እስራኤል በሮማዊያን ቅኝ ግዛት ውስ ጥ ነበረች።ሰዱቃውያን ሰርኧዲን በሚባል ምክር ቤት ውስጥ 70 መቀ መጫ ነበራቸው፤ሰዱቃውያን በእስ ራኤልና በሮማውያን መካከል ሰላም ና መልካም ጉርብትና እንዲኖር የሚሰሩ በላይኛው እርከን(Upper Class) ላይ የሚገኙ ቡድኖች ነበሩ።
ሰዱቃውያን የእስራኤል ሊቀ ጳጳሳት የበላይ መሪዎች በመሆን ህዝቡን በሃይማኖትም በፖለቲካም ያገለግሉ ነበር፤ ሰዱቃውያን አምስቱን በሙሴ የተጻፉትን መጽሐፍት ብቻ ነበር የሚ ቀበሉት ሌላውን የብሉይ ኪዳን ቅዱ ሳት መጻህፍት አይቀበሉም። ሰዱቃ ውያን የኢየሱስ ክርስቶስ አገልግሎት ቀንደኛ ተቃዋሚዎች ነበሩ፣ሲሰብክ ስብከቱን ይተቻሉ፣ ተአምር ሲሰራ በአጋንንት ስም ነው አጋንንት የሚያወ ጣው ይላሉ፣ሲፈውስ አይቀበሉም፣ የእነርሱ ስራ የመንፈስ ቅዱስን ስራ ዝም ብሎ መቃወም ነው፤ነገር ግን ሃይል አልባ የሃይማኖት ስልጣናቸ ው፣ ተቃውሟቸው በኢየሱ ስ ላይ ምንም ለውጥ አላመጣም ነበር፣ በዚህም ዘመን የሰዱቃዊያን አይነት ማንነት ያላቸው አልጠፉም፣ አገል ጋች ን የማሳደድ ፕሮግራም እና ስትራቴ ጂ አውጥተው የሰይጣን ቀኝ እጅ የሆኑ በየመንደሩ በየህብረቱ የተሰገሰጉ እውነተኛ ወንድሞች የሚመስሉ ግን ያይደሉ ብዙዎች ናቸው
”የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ።”
2ጢሞ 3 : 5
የዘመኑ ሰዱቃውያን አነጣጥረው በቤተክር ስቲያን ውስጥ የሚቃወሙ ት 9ኙ ዋና ዋና የመንፈስ ቅዱስ ስራዎችና ስጦታዎች:–
1,የነብያትን አገልግሎት ከቤተክርስትያን ውስጥ ማዳከም
2,የፈውስና የተአምራት አገልግሎቶ ችን ማናናቅ
3,አጋንንት የማውጣት ስጦታዎችን የውሸት ትእይንት አድርጎ መስበክ ፣ማውራት፣ማናፈስ
4,አምስቱን ቢሮዎች ከቤተክርስቲያን ውስጥ አስወግዶ ቤ/ክንን ባዶ ማድረግ፣(ሐዋርያ፣ነብይ፣መጋቢ፣አስተማሪ፣ወንጌላዊ)
5,ከመንፈስ ቅዱስ ሃሳብ ጋር የማይሄድ አስተሳሰብ፣አመራር በቤ/ክ ውስጥ መዘርጋት፣
6,ሀይል አልባ ቲኦሎጂ ማስፋፋት
7,ትንቢትን መናቅና ማናናቅ፣
8,ሚዛናዊነት የጎደለው አመለካከት ማስፋፋት ነው።
2,ከዘረኝነት
ዘረኝነት በአጥቢያ ቤተክርስቲያን ውስጥ ሲገባ የሚከሰቱ 30ዋና ዋና አደጋዎች;-
1,ቤተከርስቲያን ሰማያዊ የሆነውን፣ ከሰማይ የተቀበለችውን አዲሱን ማንነት ትታ ስጋዊ በሆነው ምድራዊ ማንነት ብቻ በመመላለስ አዱሱን ፍጥረት ችላ ማለት ውስጥ ትገባለች 2,ቤተከርስቲያን ትልቁን የክርስቶስ ኢየሱስን ተልእኮ ጥላ/ዘንግታ በራሷ የስጋ ጉዳይ መጠመድ ትጀምራለች።
3,አሮጌ ፍጥረት/ስጋዊነት በቤተከር ስቲያን ውስጥ ይሰለጥናል።
4,ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ ስልጣኗን እንዳትጠቀም አቅም ታጣለች።
5,ቤተክርስቲያን የመንፈስ ቅዱስ ፍሬ ማፍራት ትታ የስጋ ስራዎች ውስጥ ትጠመዳለች።
7,ቤተከርስቲያን ሰዎች እንዳይድኑ መሰናከያ ልትሆን ትችላለች።
8,የእግዚአብሔርን ቁጣ ትቀሰቅሳለች
9, ቤተከርስቲያን ንጹህ አምልኮ ለእግዚአብሔር ማቅረብ ይሳናታል።
10,ቤተከርስቲያን መፈራረስ ውስጥ ትገባለች።
11,በዘረኝነት ላይ ያተኮረ አደረጃጀት ፣አስተምህሮ፣ስብከት፣አገልግሎት ላይ ትወድቃለች።
12,በመጨረሻው ቀን ከስራ ሽልማት ትጎድላለች።
13,ቤተከርስቲያን የሃይልና የስልጣን አካል/ድርጅት ከመሆን ይልቅ ባዶ ትሆናለች
አራተኛ ክፍል
ቤተክርስቲያን መጠንቀቅ ካለባትና ነቅታ ልትከላከል ከሚገባት አደጋዎ ች አንዱ የኤልዛቤል አሰራር ነው።
3,ከኤልዛቤል አሰራር
# ኤልዛቤልና አሰራሯ
””ዳሩ ግን። ነቢይ ነኝ የምትለውን ባሪያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ስለምትተዋት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤””’
የዮሐንስ ራእይ 2 : 20
ኤልዛቤል
1, ጣኦት አምላኪ ሴት ነች
2,ነፍሰ ገዳይ ሴት ነች።
3 የባልን ራስነት የማትቀበል ሴት ነች
4 ልበ ደንዳና ሴት ነች።
5 ጋለሞታ ሴት ነች።
6 ባለቤቷን የምትነዳ ሴት ነች
(1ነገ 20:25)።
7 ክፉ መካሪ ነች።
8 ስነምግባር የሌላት ሴት ነች።
9 መተተኛ ሴት ነች።
10 ጨቋኝ ንግስት ነች።
11 ሐሰተኛ ነብይ ነች።
12 ሐሰተኛ አስተማሪ ነች።
13 ሴረኛ ሴት ነች።
14 ነብያትን የምታሳድድ ጠላት ነች።
15 ራስ ወዳድ ሴት ነች።
16 ፍትህ የምታጣምም ሴት ነች።💢የኤልዛቤል አላማ1, የእግዚአብሔርን ህዝብ ለጣኦት እንዲገዙ ማድረግ።
2,የእግዚአብሔር ህዝብ እንዲሴስኑ ማድረግ።
ኤልዛቤል 👉ጋለሞታ ሴት ነች
የጋለሞታይቱ ሴት ምልክቶች
ምሳሌ 7:
💢ኤልዛቤል የተለየ ሰውን ሁሉ የሚስብ የአለባበስ መንገድ አላት ምሳሌ 7;10
💢ኤልዛቤል ዘዋሪ አጥፊ ነች
” ሁከተኛና አባያ ናት፥ እግሮችዋም በቤትዋ አይቀመጡም፤ምሳሌ 7:11
💢 ኤልዛቤል አዳኝ(የምታድን) ሴት ነች። ”’አንድ ጊዜ በጎዳና፥አንድ ጊዜ በአደባባይ፥ በማዕዘኑም ሁሉ ታደባለች።” ምሳሌ 7 : 12
💢 ኤልዛቤል ማንንም አታፍርም።
”ያዘችውም ሳመችውም፤ ፊትዋም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው።”
ምሳሌ 7 : 13
💢 ኤልዛቤል ከማንም ጋር አካላዊ ንኪኪ ትወዳለች ምሳሌ 7 : 13
💢 ኤልዛቤል እቤት አትቀመጥም እግሮችዋም በቤትዋ አይቀመጡም፤
ምሳሌ 7 : 11
💢 ኤልዛቤል ስለ ህይወት ደንታ ቢስ ነች።
”’ እግሮችዋ ወደ ሞት ይወርዳሉ፥ አረማመድዋም ወደ ሲኦል ነው፤ ”’
ምሳሌ 5 : 5
💢 ኤልዛቤል ጥፋቷን የማትቀበል አማፂ ነች
”’እንዲሁ በልታ አፍዋን የምታብስ። አንዳች ክፉ ነገር አላደረግሁም የምትልም የአመንዝራ ሴት መንገድ ናት። ”’ ምሳሌ 30 : 20
💢 ኤልዛቤል ሃይማኖታዊ ሆና መታየት ደስ ይላታል ።
”’ መሥዋዕትንና የደኅንነት ቍርባንን ማቅረብ ነበረብኝ፤ ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ።”’ ምሳሌ 7 : 14 ✴
💢 ኤልዛቤል ገዳይ ነች።
”ወግታ የጣለቻቸው ብዙ ናቸውና፤ እርስዋም የገደለቻቸው እጅግ ብዙ ናቸው። ”” ምሳሌ 7 : 26 💢 ኤልዛቤል ሙልጭልጭ እና ብልጣ ብልጥ ነች።
💢ኤልዛቤል ውበቷን በመጠቀም ታጠምዳለች። ውበትዋን በልብህ አት ውበትዋን በልብህ አትመኘው፤ ሽፋሽፍትዋም አያጥምድህ።
💢ኤልዛቤል በንግግር ታጠምዳለች
”” ከጋለሞታ ሴት ከንፈር ማር ይንጠባጠባልና፥ አፍዋም ከቅቤ የለሰለሰ ነውና፤”” ምሳሌ 5
💢ኤልዛቤል ለወሲብ ግብዣ ታደርጋለች።
”’ና፥ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፥ በተወደደ መተቃቀፍም ደስ ይበለን።”
ምሳሌ 7 : 18💢የኤልዛቤል አስተምህሮ
1, ድህረ ዘመናዊነት/post modernism ይህ አስተሳሰብ እና ፍልስፍና በአንድ መንገድ ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን ዘርፈ ብዙ በሆኑ መንገዶች የሚገለጽ ነውቤተክርስቲያን ነቅታ ልትጋደል የሚገባት ሌላኛው የዘመኑ ተግዳሮት
የኤልዛቤል አሰራርና አስተምህሮ ነው።
የኤልዛቤል አስተምህሮ
1, ድህረ ዘመናዊነት/post modernism ይህ አስተሳሰብ እና ፍልስፍና በአንድ መንገድ ብቻ የሚገለጽ ሳይሆን ዘርፈ ብዙ በሆኑ መንገዶች የሚገለጽ ነው። ለምሳሌ በስነጽሑፍ፣በዘፈን፣በፊልም፣በፋሽን ፣በቴክኖሎጂ፣በትምህርት እና በማህ በራዊ ሚዲያዎች የሚቀነቀን ወይም የሚሰበክ የኤልዛቤል አስተ ምህሮ ነው። ድህረ ዘመናዊነት/post mod ernism አለም አቀፍ እውነት የለም ብሎ የሚያምን ዘመናዊ አመለካከት ነው። እውነት የሚባለው ሰዎች የተስማሙበት እንጂ በራሱ የቆመ ነገር አይደለም ይላሉ።በዚህ አስተምህሮ እውነት ፍጹም ሳይሆን አንጻራዊ፤እውነት በቦታ፣ በሁኔታ በጊዜ ምክንያት የሚለዋወጥ ነው። ✳
ድህረ ዘመናዊነት/
post modernism/ በክርስትና ላይ ያመጣው ተጽእኖ
✔አለማዊነት
✔ቁሳዊነት
✔ሰውን ያማከለ አመለካከት መስበክ
✔ፍትወትን ማስፋፋት።
✔ሳይንስን የሁሉ ነገር ምንጭ ማድረግ
✔የፍቅር መቀዛቀዝ።
✔የእግዚአብሔር ቃል ከአለም ጋር ማቻቻል።
💢ይሄ ሁሉ በዘመናችን ቤተክርስቲ ያን በግልጽ እያየን ያለ የኤልዛቤል አስተምህሮ ውጤት ነው። በአለም ላይ ያለች ቤተክርስቲ ያን የተለያዩ የሐሰት ትምህርት እየተገዳደራት ይገኛል።
✔ ✔ ✔
ሌሎች የኤልዛቤል ትምህርቶች
👉አምላክ የለሽነት atheism
ይህ አስተምህሮ ሰው ሊያምን የሚገባው የሚታየውን እና የሚዳሰሰውን ብሎ ያስተምራል።
👉 ዳርዊኒዝም/ Darwinism /
ኢቮሊሽነሪ ቲዎሪ) ይህ አስተምህሮ እግዚአብሔር መኖሩን ይክዳል ፣እውነት በሳይንስ መረጋገጥ አለበት ይላል። አምላክ የለም ፣ሰው ከእንስሳ የተገኘ እንስሳ ነው ይላል ።
👉ናቹራሊዝም / naturalism
ይሄ የኤልዛቤል አስተምህሮ የሰው ልጅ ሙሉ በሙሉ ትኩረቱን በምድር ላይ ማድረግ አለበት።ይላል ።””’
👉 ማቴሪያሊዝም/ materialism
ይህ አስተምህሮ ማንኛውም እውነት መረጋገጥ ያለበት ለፊዚክስ ቅድሚያ በመስጠት፣ በሳይንስና በቴክኖሎጂ ነው ብሎ ያስተምራል። ኤልዛቤል ማነች?

ኤልዛቤል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ 23 ጊዜ የተጠቀሰች ሲሆን 22 ጊዜ በብሉይ ኪዳን 1 ጊዜ በአዲስ ኪዳን ውስጥ ተጠቅሳለች። ኤልዛቤል ከጣዖት አምላኪ ቤተሰብ የተወለደች ጣኦት አምላኪ ነች; ኤልዛቤል ማለት ሐሰተኛ አስተማሪ ወይም አሳች የሚል ትርጉም አለው። የሲዶናዊያን ንጉስ የኤትበአል ልጅ ነበረች። አባቷ ኤትበአል የበአል አምልኮ ተከታይ ነበር። ኤልዛቤል የእስራኤላውያን ንጉሥ የሆነው የአክአብን ሚስት ነበረች። ኤልዛቤል እና አክአብ ወደ ንግስና ከመጡ በኋላ ለእስራኤላው ያን የውድቀት እና የመንፈሳዊ ጨለምተኝነት፣የሞራል ውድቀት ምክንያት ሆነዋል።

በምድር ላይ ያለ እያንዳንዱ በክርስቶስ ኢየሱስ አምኖ የዳነ ክርስቲያን ወደ ሰማይ እስከሚሄድ ድረስ በምድር ላይ መንፈሳዊ ውጊያ ያካሂዳል።ይህ ውጊያ ከደም እና ከስጋ ጋር ሳይሆን መንፈሳዊ ነው። ስለሆነም እያንዳንዱ እንቅስቃሴ በመንፈስ የሚደረግ እንጂ በስሜት ተገፋፍቶ የሚደረግ ውጊያ አይደለም። እንደ አማኝ በምድር ላይ አሸናፊዎች ፣ ብርቱዎች፣ገዢዎች ፣አስፈሪዎች፣ ሆነን በክርስቶስ ተፈጥረናል። የተደረግነውን ማንነት በመጠቀም የዲያብሎስን ስራ ማፈራረስ የቤተክርስቲያን ድርሻ ነው። መንፈሳዊ ውጊያ የምናደርገው ሰይጣንን ለማሸነፍ ሳይሆን አሸናፊነታችንን ለማረጋገጥ ነው።

Leave a comment