በአዳማ ከተማ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ስካይ ሲቲ ሆቴል ተመረቀ

ስካይ ሲቲ ሆቴል

የካቲት 12/2014 (ዋልታ) የአዳማ ከተማን ተመራጭ የቱሪስት እና ኮንፈረስ ከተማ ለማድረግ የተያዘውን ውጥን ለማሳካት ተደማሪ አቅም የሚሆነው ስካይ ሲቲ ሆቴል ተመረቀ።

ሆቴሉ በ100 ሚሊዮን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን ዘመናዊ የሆቴል አገልግሎትን ከባህላዊ ጋር በማጣመር አገልግሎት ይሰጣል ተብሏል።

የሆቴሉ ባለቤት ገነነ ነጋሽ ሆቴሉ ለአዳማ ከተማ ሌላ ተጨማሪ መስኅብ መሆኑን ገልፀው አሁን በጀመረው አገልግሎት እና በቀጣይ ማስፋፊያው ለበርካታ ሰዎች የሥራ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል።

አሳየናቸው ክፍሌ (ከአዳማ)